የአሚኮን 30ኛ ዓመታት የምሥረታ በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀው አውደ ርዕይ ተከፈተ።

34
ባሕር ዳር: ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአሚኮን 30ኛ ዓመታት የምሥረታ በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀው አውደ ርዕይ ተከፍቷል።
አውደ ርዕዩ የአሚኮን የ30 ዓመታት ጉዞን፣ ውጣ ውረዶችን፣ ያለፈባቸው ምዕራፎችን እና ዕድገቱን የሚያሳይ ነው። በአውደ ርዕዩ የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ.ር)፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ እና የአሚኮ የሥራ አመራር ቦርድ አባል መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር)፣ የጋምቤላ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ ኡጅሉ ጊሎን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የሥራ ኀላፊዎች እና እንግዶች ተገኝተዋል።
አሚኮ የተመሠረተበትን 30ኛ ዓመታት የምሥረታ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው። አሚኮ በ30 ዓመታት ጉዞው በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ታላቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ከፍ እንዲል፣ የሕዝብ አንድነት እንዲደረጅ ያደረገ ታላቅ ተቋም ነው።
አሚኮ በ30 ዓመታት ጉዞው በሀገር አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ ከኾኑ ሚዲያዎች መካከል አንደኛው ኾኗል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleቆልማማ እግር (clubfoot) በሕክምና የሚስተካከል ችግር ነው።
Next article“አሚኮ የማይቻሉ የሚመስሉ ፈተናዎችን አልፎ ለስኬት የበቃ ተቋም ነው” ምክትል አፈጉባኤ አማረ ሰጤ