
የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና በባሕር ዳር ከተማ ተጀመረ፡፡
ባሕር ዳር: ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ወደ ተምሳሌት ሀገር በተሻገረ ህልም እና በላቀ ትጋት፤ አስተማማኝ ነገን መሥራት” በሚል መሪ ሃሳብ ለክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የሚሰጠው ሥልጠና በባሕር ዳር ተጀምሯል፡፡
ስልጠናው እስካሁን በክልሉ በተመዘገቡ የልማት እና መልካም አስተዳደር ሥራዎች አፈጻጸም፣ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የሚያተኩር መኾኑ ተጠቁሟል፡፡
በወቅታዊ ክልላዊ፣ ሀገራዊ፣ አሕጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያተኩረው የመሪዎቹ ስልጠና ለተከታታይ ቀናት ይሰጣል ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!