
በትንሿ ኢትዮጵያ፣ በበረሀዋ ገነት፣ በጉራማይሌዋ የፍቅር ከተማ ድሬ ገብተናል፡፡
በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን ለድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ፣ ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለከተማው ሕዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡
በቆይታችን የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጨምሮ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የሥራ ሂደት የምንመለከት ይኾናል፡፡