
ራዕያችን ግልፅ ነው። የላቀ የግንባታ አቅም የፈጠረች፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነች እና ለትውልዱ አሻራዋንና የዕድገት ትሩፋቷን የምታወርስ ኢትዮጵያን መገንባት ነው። መንግሥት ለዚህ የልዕልና ህልም መሳካት ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ጨምሮ ብሔራዊ የልማት ዕቅዶችን እየተገበረ ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም ጠንካራ ሀገር የመገንባት ጉዟችንን ለማሳካት የ25 ዓመታት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭን ይፋ አድርገናል። ይህ ኢኒሼቲቭ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለመገንባት የሚያስችል፣ ቁልፍ ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ተግዳሮቶችን በጋራ የሚፈታም ጭምር ነው።
በተደመረ አቅም፣ በባለሙያዎቻችን እውቀት፣ በተቋሞቻችን ቅንጅት እና በመንግስት የተሟላ ድጋፍ ኢትዮጵያን የአህጉራችን የልህቀትና የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የጀመርነውን ጉዞ በስኬት ለማጠናቀቅ በትጋት እንሰራለን።