
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጣና ሐይቅ ላይ ዘመናዊ የባሕር ትራንስፖርት እና የቱሪዝም አገልግሎት ለመስጠት በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፋ ባሕር ዳር ከተማ የገባችው ጣናነሽ ፪ ጀልባ ዛሬ በጣና ሐይቅ ዳርቻ አርፋ ወደ ሐይቁ ለመግባት ተዘጋጅታለች።
የየብስ ጉዞዋን በኢትዮጵያውያን ፍቅር እና አንድነት ታጅባ የፈጸመችው ጣናነሽ ፪ በጣና ዳርቻ ላይ ቆማለች። ለዘመናት ውበትን፣ ታሪክን እና ሃይማኖትን ይዞ ለኖረው ጣና ሐይቅ ተጨማሪ ውበት ናት።
ጀልባዋ በቅርብ ቀን በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ወደ ጣና ሐይቅ ገብታ አገልግሎት እንደምትሰጥም ተገልጿል።
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን