የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ነገ ይጀምራል።

72

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ‎የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ከሐምሌ 19/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 23/11/2017 ዓ.ም በባሕር ዳር ይካሄዳል።

ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆየውን መደበኛ ጉባኤ አስመልክቶ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

በጉባኤው የመጀመሪያ ቀን ውሎ የ2017 በጀት ዓመት የአስፈጻሚው አካል የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ዋና አፈ ጉባኤዋ ጠቁመዋል።

ከአምስት ዓመቱ ስትራቴጅክ ዕቅዱ የተቀዳው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ የምክር ቤት አባላቱ ይወያይበታል።

ዕቅዱን ለማስፈጸም የተመደበው በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቦ እንደሚጸድቅም ዋና አፈ ጉባኤዋ አንስተዋል።

በጉባኤው ልዩ ልዩ ሹመቶች ቀርበው ይፀድቃሉ ያሉት ዋና አፈ ጉባኤዋ የምክር ቤት አባላቱ የሕዝብ ውክልናቸውን ለመወጣት የሚያስችል ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃልም ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለእናቶች ቀድመን መድረስ ያለብን ሴቶች ነን”
Next articleየአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።