ብቁ እና ተወዳዳሪ የሰው ሃብት ማፍራት ለዘላቂ ሰላም እና እድገት መረጋገጥ ወሳኝ ነው።

9

እንጅባራ: ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ክልላዊ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ሥልጠና በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር እንጅባራ ከተማ እየተሰጠ ነው።

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት በቢሮ ኀላፊ ደረጃ የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ አማካሪ ሽቤ ክንዴ ለዘላቂ ሰላም እና እድገት መረጋገጥ ብቁ እና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ማፍራት ቁልፍ ጉዳይ መኾኑን ተናግረዋል።

መንግሥት በትምህርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችሉ የትምህርት ሪፎርም ሥራዎችን እየሠራ ነው ያሉት አማካሪው ለሪፎርም ሥራዎቹ ተግባራዊነት የመምህራን እና የትምህርት አመራሮች ኀላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የብሔረሰብ አሥተዳደደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ደስታው ዓለሙ ሥልጠናው የመምህራንን እና የትምህርት ቤት አመራሮችን አቅም በማጎልበት የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዝ መኾኑን ተናግረዋል።

ለ13 ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው በዚህ ሥልጠና ከአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር፣ ከሰሜን ጎጃም እና ከባሕር ዳር ከተማ የተውጣጡ 1 ሺህ 585 የመካከለኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህር ቤት አመራሮች ተሳታፊ መኾናቸውን ኀላፊው ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article‎ጣናነሽ ቁጥር ፪ ጀልባ ደጀን ከተማ ደረሰች።
Next articleበእውቀት የዳበረ እና ችግሮቹን በሠለጠነ መንገድ የሚፈታ ማኅበረሰብ ለመገንባት ትምህርት ቀዳሚው መሳሪያ ነው።