‎ጣናነሽ ቁጥር ፪ ጀልባ ደጀን ከተማ ደረሰች።

298

ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ተጨማሪ ከፍታ የኾነችው ጣናነሽ ቁጥር ፪ ውጣ ውረድ የበዛበትን እጅግ አስቸጋሪ የዓባይ በርሃ ጉዞዋን ጨርሳ ደጀን ከተማ ደርሳለች።
‎
ጀልባዋ ደጀን ከተማ ስትደርስ በደጀን ወረዳ፣ በደጀን ከተማ አስተዳደር፣ በአዋበል ወረዳ፣ በሉማሜ ከተማ አስተዳደር እና በዞኑ የመንግሥት ከፍተኛ ሥራ ኀላፊዎች እና በአካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል።
‎
‎ለቱሪዝም ሃብት ተጨማሪ ገጸ በረከት ኾና የመጣችው ጣናነሽ ቁጥር ፪ ጀልባ ጣና ሐይቅ ለመድረስ 335 ኪሎ ሜትር ብቻ ቀርቷታል።
‎
‎በአንድ ጊዜ 188 ሰዎችን የማጫን አቅም ያላት ጣናነሽ ቁጥር ፪ መዳረሻዋ በኾነው ጣና ሐይቅ እስከምትደርስ ድረስ በደረሰችባቸው አካባቢዎች ሁሉ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላት ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበበጀት ዓመቱ ከ43 ሚሊዮን ብር በላይ ከሙስናና ብልሹ አሠራር ማዳን ተችሏል።
Next articleብቁ እና ተወዳዳሪ የሰው ሃብት ማፍራት ለዘላቂ ሰላም እና እድገት መረጋገጥ ወሳኝ ነው።