“በመትከል ማንሠራራት ጉዞ ላይ ነን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

39

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ “ዛሬ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ ሀገር ለማስረከብ ከነገ ሀገር ተረካቢ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የክልሉ እና የባሕር ዳር ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የአረንጓዴ አሻራችንን አኑረናል” ብለዋል።

የአረንጓዴ አሻራችን እንደሀገር የውበት ምንጭ የኢኮኖሚ ተደማሪ አቅም እንዲሆን ታቅዶ የሰራነው ሥራ በውጤት ፍሬ አፍርቶ መታየቱን ገልጸዋል።

በባሕርዳርም የአረንጓዴ አሻራ ሥራ በዘንባባዎች እና በልምላሜዎቿ የተዋበችውን ከተማ ይበልጥ የተዋበች እና ምቹ ዓለማቀፍ መዳረሻ የሚያረጋት ይሆናል ነው ያሉት።

ለሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራችን በተባበረ ክንድ እንትጋ በማለትም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

Previous articleእውነተኛ ዳኛ ካለ እንኳን ባላንጋራ ወንዝም ይረታል የሚል ብሂል ያለው ሕዝብ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleእርስዎ በዓመት ስንት ጊዜ ቅድመ ምርመራ ያደርጋሉ?