ስኬታማ የልማት ፕሮጀክቶችን አሠራር መዋቅራዊ አድርጎ ማስቀጠል ይገባል።

17

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል።

የከተማ አሥተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የልማት ፍላጎት እና ማኅበራዊ አገልግሎት ማፋጠን የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን መገንባት ችለናል ብለዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ 15 ሺህ 960 ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ችለናል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ጎስቋላ ገፅታ በመቀየር ለኑሮ ምቹ እና ለቱሪዝም ሳቢ ማድረግ የቻለ የልማት ፕሮጀክት መኾኑን ገልጸዋል።

በአምራች ዘርፉ የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ፕሮግራም ትልቅ ተዕፅኖ በማምጣት ኢንዱስትሪዎች ያለባቸውን የተወሳሰበ አሠራር መቅረፍ እና የማምረት አቅማቸውን የመጨመር ሥራ ሠርተናል ነው ያሉት።

ገቢን አሟጥጦ ለመሠብሠብ የታቀደው እቅድ የተሳካበት፣ የተሰበሰበው ገቢ ለዘላቂ ልማት የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያጎላ እና 71 በመቶውም ለድህነት ቅነሳ የዋለበት ነው ብለዋል።

በዚህ መድረክም ያልተፈቱ ችግሮችን በመመርመር እና በመለየት እንፈታለን ነው ያሉት።

ዘላቂ ልማት እንዲኖር ሙስና፣ ጉቦ እና ተገቢ ያልኾነ የአመራር ሥርዓት መቅረፍም ይገባል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ የተሳኩ መልካም አፈጻጸሞች ዘላቂ ማድረግ እና መዋቅራዊ ሥርዓት ተክሎ ማስቀጠል እንደሚገባ አንስተዋል።

ዘጋቢ፦ አንዷለም መናን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየገቢ አሰባሰብ ዘመኑ ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበበት ነው።
Next articleጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ እየገነባ መኾኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።