
አዲስ አበባ: ሰኔ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባንኩ አጠቃላይ ሃብት ከ15 ቢሊየን ብር በላይ ከፍ ማለቱን ባንኩ አስታውቋል።
የሂጅራ ባንከ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዳውድ ቀኖ አባገሮ ሂጅራ ባንክ በ2024/25 የበጀት ዓመት የሦስተኛ ዓመት የዕድገት ስትራቴጂ በትግበራ ሂደቱ ስኬታማ ውጤት በማስመዝገብ ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ ማግኘቱን ገልጸዋል።
ይህም ባንኩ ባለፈው ዓመት ካስመዘገበው ጠቅላላ ገቢ 148 በመቶ ዕድገት ማሳየቱንም አንስተዋል። ከ840 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍም ማግኘቱን ጠቁመዋል። የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ወደ 12 ቢሊዮን ብር በማሳደግ ስኬታማ መኾናቸውን ተናግረዋል።
ባንኩ የማክሮ ኢኮኖሚ ነባራዊ ሁኔታዎችን ተፅዕኖ በመቋቋምም፣ ተደራሽነቱን በማስፋት 135 ቅርንጫፎችን መከፍቱንም አንስተዋል። በ2024/2025 በጀት ዓመት 35 አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉንም ገልጸዋል።
ሂጅራ ባንክ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኦምኒ ፕላስ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች ከ350 ሺህ በላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል።ባለፉት 6 ወራት ብቻ የሀላል ፔይ ዋሌት ተጠቃሚዎች ከ811 ሺህ በላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።
የባንኩ አጠቃላይ ሃብት በበጀት ዓመቱ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ 15 ቢሊዮን ብር ማለፉን ተናግረዋል። የተቀማጭ ገንዘብ መጠንም ወደ 12 ቢሊዮን ብር በማሳደግ ስኬታማ ሥራ መሥራቱን አንስተዋል።
ዘጋቢ:- አፈወርቅ አበዶም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!