ስለሀገር እየመከሩ፤ ስለሰላም እየተጣሩ ነው።

15

ባሕር ዳር: መጋቢት 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል።

መርሐ ግብሩ ከመጋቢት 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ዘላቂ ሰላምን ያመጣሉ፤ ሀገርን ከፍ ያደርጋሉ፤ ለጋራ እድገትም ይበጃሉ የተባሉ ሃሳቦች እየተውጣጡበት ነው።

ስለ ሰላም ብለው፣ ስለ ሀገር አስበው እና ስለ ሕዝብ ተጨንቀው ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በመነሳት በባሕር ዳር የተገኙ የሕዝብ ልጆች አሉ የተባሉ ችግሮችን እያነሱ እየተወያዩ ስለመኾኑ ገልጸውልናል።

ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝብ ሃሳብ ማዋጣት የታሪክ ባለቤት እንደመኾን ነው፣ ደስታ እንጅ ድካም አይሰማንም ከጥዋት እስከ ማታ እየተመካከርን ነው ብለዋል።

ችግሮችን በግልጽ አንስቶ መመካከር እና ለሀገር የሚበጅ ሃሳብ አምጦ መውለድ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ ኀላፊነት ነው። በመኾኑም በዚህ የምክክር ሂደት ውስጥ ሁሉም ሃሳቡን እንዲያዋጣ እና ከመፎካከር ወጥቶ መመካከር እንደሚቀድም ጥሪ አቅርበዋል።

የሕዝብ ወኪሎች የተነሱ አጀንዳዎችን በመለየት እና በመሰነድ በቀጣይነት ለምክክር ኮሚሽኑ ገቢ እንደሚያደርጉም ይታወቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክት፦
Next article“ቀጣይ ወራት ሥራዎችን በጥራት እና በፍጥነት የምናከናውንባቸው ጊዜያት ናቸው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ