የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ለአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ አዲስ አበባ ገቡ።

346

አዲስ አበባ: የካቲት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በምታስተናግደው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመታደም ነው የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዝዳንቱም ለተደረገላቸው አቀባበል ምሥጋና አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ ሰለሞን አሰፌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ጋር በመሆን ለሱዳን ሕዝብ የሰብዓዊ ድጋፍ ከፍተኛ ኮንፈረንስ በጋራ በማዘጋጀቷ ደስታ ይሰማታል።
Next articleምክር ቤቱ የዳኞችን ሹመት አጸደቀ።