የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ አዲስ አበባ ገቡ።

32

አዲስ አበባ: የካቲት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።

ዘጋቢ፦ ሰለሞን አሰፌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleምክር ቤቱ የቀረቡለትን ረቂቅ አዋጆች መርምሮ አጸደቀ።
Next articleኢትዮጵያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ጋር በመሆን ለሱዳን ሕዝብ የሰብዓዊ ድጋፍ ከፍተኛ ኮንፈረንስ በጋራ በማዘጋጀቷ ደስታ ይሰማታል።