ንጋት ኮርፖሬት ከ1 ነጥብ 792 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

115

ባሕር ዳር: የካቲት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የንጋት ኮርፖሬት የሥራ አፈጻጸም በአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4 ዓመት የሥራ ዘመን፣ 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ቀርቧል።

የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የኮርፖሬቱ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አምላኩ አስረስ (ዶ.ር) ተቋሙ በበርካታ ዓለም አቀፍ እና ሀገራዊ ፈተናዎች ውስጥም ኾኖ ውጤታማ ቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት እያካሄደ ነው ብለዋል።

ኮርፖሬቱ በአጠቃላይ በ28 ተቋማት ላይ የኢንቨስትመንት ሃብት መድቦ እንደሚያንቀሳቅስም ጠቅሰዋል።

ሥራ አሥፈጻሚው ከዘረዘሯቸው የኮርፖሬቱ ዋና ዋና አፈጻጸሞች መካከል:-

👉 የኮርፖሬቱ ጠቅላላ የምርት ሽያጭ ገቢ 10 ቢሊዮን 250 ሚሊዮን 949 ሺህ ብር ደርሷል፤ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ1 ነጥብ 87 ቢሊዮን ብር እድገት አሳይቷል።

👉 1 ቢሊዮን 792 ሚሊዮን 18 ሺህ ብር የተጣራ ትርፍ አግኝቷል፣ ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ6 ነጥብ 08 በመቶ እድገት አሳይቷል።

👉 ሙሉ በሙሉ ባለቤት ከኾነባቸው ኩባንያዎች ብቻ 540 ሚሊዮን 934 ሺህ ብር የትርፍ ግብር በታማኝነት ከፍሏል።

👉የክልሉን የገበያ ጉድለቶች ለመሙላት በአጠቃላይ 1 ነጥብ 25 ቢሊዮን ብር የዋጋ ግምት ያላቸው ሸቀጦችን በማቅረብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ ሠርቷል።

👉 71 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወጭ በማድረግ ለትምህርት፣ ለጤና እና ለተለያዩ ማኅበራዊ ኀላፊነቶችን ተወጥቷል።

👉 በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በየክልሎች አጓጉዟል፣ በዚህም “የግብርና ልማት አጋር” ተብሎ የወርቅ ዋንጫ ተሸልሟል

👉 ሰሊጥ እና እጣን ለውጭ ገበያ በማቅረብ 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አግኝቷል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንት አባንግ ኩሙዳን የተመራ ልዑክ በባሕር ዳር ጉብኝት እያደረገ ነው።
Next article“ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘው ሀገራዊ የፓናል ውይይት በቡታጅራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።