
ባሕርዳር: ጥር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸሙን ገምግሟል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ሥራ አስፈጻሚ ዘመን ጁነዲ ባለፉት ስድስት ወራት 597 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና መግባታቸውን አስታውቀዋል።
ከ80 በላይ የተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ኮርፖሬሽኑ ወደ ሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች መሳባቸውን ገልጸዋል ። በተሳቡት ኢንቨስትመንቶች 14 የማምረቻ ሼዶች እና ከ70 ሄክታር በላይ የለማ መሬት ለባለሃብቶቹ መተላለፋቸውን ተናግረዋል።
ኢንቨስትመንቶቹ በኮምቦልቻ፣ በመቀሌ ፤ በቦሌ ለሚ፤ በቂሊንጦ፤ በድሬዳዋ ልዩ ነፃ ንግድ ቀጣና ፤ በጅማ እና ሰመራ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚሰማሩ መኾናቸውንም አመላክተዋል።
ባለሀብቶቹ ከሀገር ውስጥ ባለፈ ከቻይና፣ ከሩሲያ እና ከቬትና የተሳቡ መኾናቸው ተገልጿል።
ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ባለሀብቶቹ በፋርማሲዩቲካል ፤ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣፣ ቡና እና ሻይ ፤በኤሌክትሪክ መኪና መገጣጠም እና በሌሎች የቴክኖሎጂ እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ላይ ይሠማራሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!