ግሮክ – የሰው ሠራሽ አስተውሎት

67

ባሕር ዳር: ጥር 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ግሮክ የተለያዩ ተግባራትን ለማከናወን የሚያግዝ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያ ነው። ለጥያቄዎች መልስ መስጠት፣ የሒሳብ ስሌቶችን ማስላት፣ ምስል ማመንጨት እና የመሳሰሉ ተግባራትን በቀላሉ በሚቀርብለትን የጽሑፍ ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል። በጽሑፍ የሚቀርበው ጥያቄ ወይም የትዕዛዝ መመሪያ ፕሮምት ይባላል።

ንብረትነቱ የዓለማችን ባለሃብት ኤለን መስክ የኾነው ኤክስ ማኅበራዊ ሚዲያ በቅርቡ ያካተተው ይህ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያ ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት በተለያዩ የቅድመ ልምምድ ሂደቶችን አልፎ እና የትክክለኛነቱ ደረጃ በባለሙያዎች ተገምግሞ ወደ ተግባር የመጣ ነው።

የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም በአጽናፈ ዓለም ስላለ የትኛውም ጉዳይ የጋራ አረዳድ ግንዛቤ ለማግኘት የምንችልበት አማራጭ ነው። ግሮክ ራሱን የቻለ መተግበሪያ ያለው ሲኾን በኤክስ የማኅበራዊ ሚዲያ ላይም ተጨምሮ መጥቷል። በኤክስ አማራጭ ማንኛውም ሰው ይህን መጠቀም ይቻላል።

እስከ አሁን ከተፈጠሩ በፕሮሞት ወይም የጽሑፍ ጥያቄ የሚሠሩ አስተውሎት ያላቸው አማራጮች በተለየ ሁኔታ አሁናዊ (Real-time) መረጃዎችን በኤክስ ገጽ የሚለጠፉ ይዘቶች በተለጠፉበት ሰዓት ወዲያውኑ ጠይቀን ስለ ይዘቶቹ ምላሽ ማግኘት እንችላለን።

ግሮክ በፕሮሞት ከመሥራት ባለፈ የተለያዩ የድጋፍ አማራጮችን ያቀርባል። ስፖርት ለሚወድ ሰው የስፖርታዊ እንቅስቃሴ ዕቅድ ለማዘጋጀት የሚያግዝ አማራጭ ያቀርባል። የሚያስደስት ነገር እንዲነግረን ከፈለግን፣ ከ50 ዓመት በኋላ ዓለማችን ምን እንደምትመስል እንዲነግረን አልያም የምግብ አዘገጃጀት ማወቅ የምንፈልግ መኾኑን የሚጠይቁ አማራጮችም አሉት። የፈለግነውን አማራጭ በመጫን ከፍተን ማየት እና ተጨማሪ መረጃ ስንፈልግ ደግሞ የፕሮሞት መጻፊያው ላይ ጥያቄያችንን በማስፈር መጠየቅ እንችላለን።

ለተማሪዎች ደግሞ የተለያዩ ሒሳባዊ ስሌቶችን በቀላሉ በማስላት እገዛን ያደርጋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲከወን ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት።
Next articleየጣና ሐይቅን ህልውና ለመጠበቅ የሚሠራውን ሥራ ሁሉም እንዲደግፍ ተጠየቀ።