
አዲስ አበባ: ጥር 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዓቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በማይናማር በእገታ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። ዓለም ዓቀፍ ሕገ ወጥነት ቅርጽ ያለው የሕገ ወጥ ደላሎች ኢትዮጵያን ጨምሮ የ19 ሀገራት ዜጎችን በማይናማር፣ በታይላንድ እና በቻይና ድንበሮች ዜጎችን አግተው እያንገላቱ ይገኛሉ ብለዋል።
በጃፓን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከማይንማር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ውይይት ማድረጉን ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ ከማይንማር መንግሥት ቁጥጥር ውጭ በሚገኙ አካባቢዎች ዜጎች ታግተው የሚገኙ መኾኑ የመመለስ ሥራውን አስቸጋሪ አድርጎታል ነው ያሉት። ከሌሎች ሀገራት ጋር ጭምር በመተባበር በተደራጀ መልኩ እንድመለሱ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ያለፉት 6 ወራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 128 ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች እና ልውውጦች የተደረጉበት ስኬታማ ሥራዎች የተከናወነበት ነበር ብለዋል። በቀጣይ ኢትዮጵያ በሞቃድሾ አምባሳደሯን እንደምትሾምም ተናግረዋል። ከአንካራ ስምምነት በኋላ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በመሻሻሉ ይህ በቅርቡ ይከናወናል ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- አንዷለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!