
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ እና የእነዋሪ ከተማ አሥተዳደር ለተከታታይ ቀናት ሲያሠለጥናቸው የነበሩ የሰላም አስከባሪና የሚሊሻ አባላትን አስመርቋል።
ተመራቂዎች የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስጠበቅና ኅብረተሰቡ ልማት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ከድህነት እንዲላቀቅ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናበረክታለን ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
