
ባሕር ዳር: ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የመግባቢያ ሰምምነቱን የተፈራረሙት የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ከሰተ አድማሱ (ዶ.ር) ናቸው።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማስፋት፣ የኃይል መሠረተ ልማቶችን በመገንባት፣ የሠለጠነ የሰው ኀይል በማፍራት፣ የፋይናስ ዘርፉን በማዘመን፣ የውጭ ንግድ ሚዛንን በማስጠበቅ እና አምራች ዘርፉ ሀገራዊ ኢኮኖሚውን እንዲዘውር በማድረግ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2030 ኢትዮጵያን የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል እንድትኾን ማስቻልን ራዕይ አድርጎ እየሠራ ይገኛል።
የመግባቢያ ስምምነቱ ለሚኒስቴሩ ራዕይ ስኬታማነት ለፕሮጀክቶች ቴክኒካል ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ እንዲኹም የአፈፃፀም አቅምን ለማጎልበት ዓላማ ያደረገ ስለመኾኑ ተገልጿል። በጨርቃ ጨርቅ፣ በእርሻ ውጤቶች፣ በቆዳ፣ በኬሚካል እና ኮንስትራክሽን፣ በቴክኖሎጂ፣ በፋርማሲ ውጤቶች ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር በስምምነቱ እንደ አንድ ተግባር ተቀምጧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!