ባዮኒክ ዕይታ

40

ባሕር ዳር: ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ባዮኒክ የዕይታ ቴክኖሎጂ በሰው ልጆች 0ይን ላይ በቀዶ ጥገና የሚገጠም የዕይታ ቴክኖሎጂ ነው። በጉዳት ምክንያት የጎደለን የዕይታ ክፍል ተክቶ የ0ይን ብርሃንን ለማግኘት የሚረዳ ሰው ሠራሽ የዕይታ መሣሪያ ነው። ቴክኖሎጂው የ0ይን ዕይታቸው በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ሰዎች ያለባቸውን ችግር የሚያሻሽልም ነው።

ይህ መሣሪያ የሚገጠምላቸው ሰዎች በበሽታ ወይም በእድሜ መግፋት ምክንያት በሬቲና ላይ እክል ሲገጥማቸው የሚተገበር ነው። ሌላ ዓይነት የዕይታ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ውስንነት የሚቀርፉ ሌሎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችም በመልማት ሂደት ላይ ይገኛሉ። ሬቲና 0ይናችን የብርሃን ሞገድን እንዲለይ እና እንዲያስተላልፍ የሚያስችል ክፍል ነው። የተለያየ ተግባርን ከሚያከናውኑ ህዋሶች የተዋቀረ ነው።

ለምሳሌ ፎቶሪሴፕተር የሚባለው ህዋስ ብርሃንን ለይቶ መልዕክት ያሳልፋል። ከዛም መልዕክቱ በሬቲና የመካከለኛው የህዋስ ውቅር አድርጎ፣ ኦኘቲክ ነርቭን አልፎ አዕምሮ ላይ ይደርሳል። በመጨረሻም አዕምሮ ላይ ምሥል ይፈጠራል። የምሥል መልዕክት ወደ አዕምሮ እንዲደርስ የሚያደርጉ ህዋሶች ጉዳት ሲደርሰባቸው መልዕክቱ አዕምሮ ላይ ሳይደረስ ስለሚቀር ዕይታ ላይ ችግር ይፈጥራል።

በእድሜም ኾነ በሌላ የጤና እክል ምክንያት የፎቶሪሴፕተር ህዋስ ጉዳት ሲደርስበት የተቋረጠውን የብርሃን መልዕክት ሳይስተጓጎል አዕምሮ ላይ እንዲደርስ የሬቲና ፕሮስቴሲስ ወይም ባዮኒክ ዕይታ የተባለው ቴክኖሎጂ በምትኩ እንዲሠራ ማድረግ ይችላል። የባዮኒክ ዕይታ ቴክኖሎጂ በግለሰብ ደረጃ በሙከራ ላይ ያለ ሲኾን ሙሉ በሙሉ ውጤታማ ከኾነ በሬቲና ምክንያት የማየት እክል ላለባቸው ሰዎች አማራጭ ሕክምና መኾን የሚችል ነው።

ባዮኒክ ዕይታ ሙሉ በሙሉ ዕይታን ይመልሳል ወይ የሚል ጥያቄ ይነሳል። ይህ ቴክኖሎጂ ዕይታን ወደ ነበረበት መመለስ ወደ ሚችልበት ደረጃ አልደረሰም። ነገር ግን ሰዎች ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ እና ቁሳቁሶች ያላቸውን ቅርጽ ማወቅ እንዲችሉ ያስችላል። ያሉበት አካባቢ ሰዎች መኖር እና አለመኖራቸውን፣ መውጫ እና መግቢያ በሮችን በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ አነስተኛ ቁሳቁሶች ለምሳሌ ማንኪያ እና ሹካ ያላቸውን ቅርጾች እንዲለዩ ያግዛል። ይህ ማለት ተጠቃሚዎች አዕምሯቸው የደረሰውን መልዕክት ተርጉም ወዳለው ቁስ እንዲተረጉም እንደ አዲስ ማስተማር ይጠይቃል። በዕይታ ላይ የሚፈጠረው የስኬት ደረጃ ከሰው ሰው የተለያየ መኾኑም ተገልጿል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በአውስትራሊያ ሞናሽ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ሙሉ የዕይታ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ችግር ይመልሳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ጄናሪስ ባዮኒክ ቪዥን ሲስተም የሚባል መጠሪያ የተሰጠው ቴክኖሎጂን ወደ ውጤት እያደረሰው መኾኑን ገልጸዋል። የምርምር ሥራው በእንስሳት ላይ ውጤታማ በኾነ ሁኔታ ተገጥሞ ጥሩ ውጤት መገኘቱ ታውቋል። በእንስሳት ላይ ተደርጎ የተገኘውን ውጤት መሠረት በማድረግ በሰዎች ላይም ሙከራ እንደሚይረግ ተመራማሪዎቹ አሳውቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ።
Next article“75ኛውን ዓለም አቀፍ የጠፈር ተመራማሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያን በዘርፉ ቀዳሚ እና ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር እንጠቀምበታለን” ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ.ር)