በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለችውን የሕጻን ሄቨንን ጉዳይ እየተከታተለው መኾኑን የሴቶች አና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገለጸ።

123

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሴቶች አና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በሕጻናት መብት ጥበቃ ላይ በተለየ መልኩ የፖሊሲ አቅጣጫዎች እንዲቀመጡ እና የአሠራር ሥርዓት እንዲዘረጋ ማድረጉን ነው የገለጸው።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሚፈፀሙ ጥቃቶች የሚመዘገቡበት እና ተገቢ የኾነ ኹሉን አቀፍ አገልግሎት እንዲያገኙ የሕጻናት የመረጃ አያያዝ ሥርዓት እንዲዘረጋ እና የቅንጅት ሥራዎች እንዲጠናከሩ እያደረገ ስለመኾኑም አስታውቋል።

በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለችውን ሕጻን ሄቨንን በተመለከተ ለደረሰው ዘግናኝ ኢሰብዓዊ ወንጀል ሚኒሰቴር መሥሪያ ቤቱ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ይህንን ዓይነት የሕጻናት ጥቃት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በጽኑ እንደሚያወግዘውም ነው የገለጸው።

በተፈፀመው ወንጀል ዙሪያ የተሰጠውን ውሳኔ አስመልክቶ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚኬድበት አካሄድ አግባብ አለመኾኑንም ገልጿል።

ከፍትሕ አካላት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የሚሠራ እና የሚከታተለው ጉዳይ እንደኾነም ነው የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያውያን በመተባበር በአንድ ጀምበር ለመትከል ከታሰበው በላይ በማሳካት ሀገራችንን ማስጠራት አለብን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ
Next articleየኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሩሲያ አምራቾች እና የዘርፉ ማኅበራት ጋር አብሮ መሥራት የሚያስችል ውይይት አካሄደ።