
ባሕር ዳር: ነሐሴ 7/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ኢትዮጵያ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ በመግባት ታሪካዊ እና ትልቅ የለውጥ ምዕራፍ ላይ ደርሳለች ብለዋል።
ሚንስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበር የፍትሕ እና የፀጥታ ተቋማት ሚና የላቀ መኾኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በፕሮግራሙ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሁሉም የሀገራችን ተቋማት ጋር በጋራና በቅንጅት የሚሠራ ተቋም መኾኑን አንስተዋል።
አያይዘውም በሀገራችን እየተተገበረ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲን በተመለከተ ከፍተኛ የፖሊስ አመራሩ አስቀድሞ መረጃዎችን ማወቁ ለሕግ ማስከበር ሥራው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረው የገንዘብ ሚንስትሩ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝተው ለሰጡት ሙያዊ ትንታኔና ግንዛቤ በፖሊስ ሠራዊቱ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረባቸውን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!