በአረንጓዴ አሻራ ልማት ንቅናቄ የፍራፍሬ ተክሎች የማልማት ሥራ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ።

14

ባሕር ዳር: ነሐሴ 7/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአረንጓዴ አሻራ ልማት ንቅናቄ የፍራፍሬ ተክሎች የማልማት ሥራ ከፍተኛ ለውጥ እና ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት በዚህ ስኬታማ ሥራ ላይ ተመርኩዘን የበለጠ ውጤት ለማግኘት አሠራራችንን ማጎልበት፣ ዘዴዎቻችንን በሚያዘምኑ ፈጠራዎች ላይ መሥራት ብሎም የአካባቢ ጥበቃ እና የግብርና ሥራዎቻችንን ለማላቅ ማኅበረሰባችንን ማሳተፍ መቀጠል ይኖርብናል ነው ያሉት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ወጣቶች ሥራ ፈጣሪ እንዲኾኑ ማበረታታት እና አጋዥ ፖሊሲዎችን መቅረጽ ያስፈልጋል”ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ.ር)
Next article“ከእልኸኝነት እና የብሽሽቅ ፖለቲካ መውጣት ይገባል” የፖለቲካ ሳይንስ መምህር