በተያዘው በጀት ዓመት የመንግሥት ገቢን ማሳደግ ላይ ዋነኛ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ አሕመድ ሺዴ ገለጹ።

11

ባሕር ዳር: ነሐሴ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በተያዘው በጀት ዓመት የመንግሥት ዋነኛ ትኩረት ገቢን ማሳደግ ስለመኾኑ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ ተናግረዋል። የገቢዎች ሚኒስቴር ከመካከለኛ ግብር ከፋዮች ጋር በታክስ ሕግ ተገዥነት እና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ የመንግሥት ዋነኛ ትኩረት ከግብር የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ መኾኑን ተናግረዋል። የገቢ አሰባሰቡ ሕግና ሥርዓትን የተከተለ እንዲኾን ለማስቻል በመንግሥት የሚመራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየተሠራ ነውም ብለዋል። የሀገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ ተቋማት በጋራ እንዲሠሩም ጥሪ አቅርበዋል።

የገቢዎች ሚኒስትሯ ዓይናለም ንጉሤ በበኩላቸው የገቢ አሰባሰቡን ለማሳደግ በቀጣይ ዓመታት 5 ዋና ዋና ስትራቴጂክ እቅዶች ተነድፈው እንቅስቃሴ ተጀምሯል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ የለበሰች ሀገር ለማስረከብ አሻራችንን እናኖራለን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleየትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ አጠቃላይ የትምህርት ሥርዓቱ መፈተሽ እንዳለበት ተጠቆመ።