በአማራ ክልል ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ከ134 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ።

31

ባሕር ዳር: ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 ዕቅድ ትውውቅ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ የቢሮው ኅላፊ እንድሪስ አብዱ እንዳሉት 38 አምራች ኢንዱስትሪዎች 138 ሺህ ቶን የተጠጋ ምርት ለውጭ ሀገር ገቢያ በማቅረብ ከ136 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አስገኝተዋል።

የቢሮ ኅላፊው አክለውም ክልሉ በገጠመው የጸጥታ ችግር ምክንያት ውድመት ደርሶባቸው የነበሩ የአበባ ልማቶች ከገጠማቸው ችግር በፍጥነት ወጥተው ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አስገኝተዋል ነው ያሉት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ትግበራው የተሟላ ሀገራዊ ዕድገት ያመጣል” ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች
Next articleየነሐሴ 2016 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል ተገለጸ።