ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የልማት ሥራዎችን ማከናወኑን የባሶና ወራና ወረዳ አማራ ልማት ማኀበር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

21

ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የባሶና ወራና ወረዳ አማራ ልማት ማኀበር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ባለፉት አምስት ዓመታት ከሕብረተሰቡ በተሰበሰበ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አስታውቋል::

የጽሕፈት ቤቱ አስተባባሪ አቶ ዓለማየሁ ታደሰ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ማኀበሩ መንግሥት ያልደረሳቸውን የልማት ሥራዎች በመሥራት ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

ማኀበሩ በአምስት ዓመታት የስትራቴጅክ እቅድ ትግበራ ቆይታው ከ31 ሺህ በላይ አባላትን በማፍራት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በማሰባሰብ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን አከናውኗል ብለዋል።

ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በዋናነትም 12 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህር ቤት ግንባታ፣ የ13 ኪሎሜትር የገጠር መንገድ ግንባታ እና 1 የጤና ኬላ ግንባታዎችን ማከናወኑን አሰተባባሪው ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ዓመታትም የሕብረተሰቡን የልማት ችግር በመለየት የልማት ሥራዎችን እእንደሚያከናውን ተገልጿል፡፡

ዘጋቢ፦ ፋንታነሽ መሃመድ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበምሥራቅ ጎጀም ዞን የአንድ ቀን የኩታገጠም የስንዴ ዘር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ።
Next articleሠራዊቱ ከሚሰጠው ሀገራዊ ግዳጅ ባሻገር ኅብረተሰቡን የሚያግዙ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙ ብርጋዴል ጄኔራል ወርቅነህ ጉደታ ገለጹ።