
ባሕር ዳር: ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እና በኦላይን መሰጠት ተጀምራል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን አስጀምረዋል። የትምህርት ሚኒስትሩን ጨምሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ.ር) እና ሌሎች የትምህርት ዘርፍ ኀላፊዎች የፈተናውን ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ኀላፊዎቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ እና አብርኾት ቤተ መጽሐፍት ፈተናውን በመውሰድ ላይ የሚገኙ ተፈታኞችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ፈተናው በዛሬው እለት በመላው ሀገሪቱ በተመረጡ የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በተመሳሳይ ሰዓት መሰጠት ጀምሯል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከ700 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ተማሪዎች በወረቀት እና በኦላይን ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ቀደም ሲል መገለጹ ይታወቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!