
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሠፈሩት መልእክት “ይህ ሆስፒታል ሰፊ መጠነ ርዕይ ያላቸው የህክምና አገልግሎቶች ለመስጠት የተገነባ ነው። ገና ብዙ ርምጃ መራመድ ቢጠበቅብንም በጤናው ዘርፍ በቂ የህክምና አገልግሎት ለዜጎቻችን ለማቅረብ ሰፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ ነው። ለዜጎች መሠረታዊ የጤና አገልግሎት በማቅረብ ሥራ ለሚተጉ የጤና ባለሞያዎች ምሥጋናችንን እናቀርባለን። የጤና ጥበቃ ሥርዓታችንን ለማዘመን በምናደርገው ያላሰለሰ ጥረት ቀጣይ አስተዋፅዖችሁ እና አገልግሎታችሁ እጅግ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!