የ2017 የፌዴራል መንግሥት በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ኾኖ ጸደቀ፡፡

56

ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡ ምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ተወያይቶ አጽድቋል፡፡ የፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ኾኖ ጸድቋል፡፡

በጀቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እድገትን ለማፋጠን ታሳቢ ያደረገ መኾኑ ተመላክቷል፡፡ የሚጸድቀውን በጀት በሕግ እና ሥርዓት የመጠቅም ኀላፊነት እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡ ምክር ቤቱ የቁጥጥር እና የክትትል ሥራውን አጠናክሮ መቀጠል ይጠበቅበታልም ተብሏል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው፡፡
Next article“መንግሥት ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚነሱ ችግሮችን በሰላም ለመፍታት ይሠራል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)