
ደብረ ብርሃን: ሰኔ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በንግዱ ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መለየት፣ የገበያ ማዕከላትን በማልማት እና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ወደ ሥራ ለማስገባት እንዲቻል ምክክር ተደርጓል። የኑሮ ውድነትን ሊያቃልሉ የሚችሉ ሃብቶች እያሉን በገበያ ማዕከላት እጥረት እና ሳይንሳዊ አሠራርን ተግባራዊ ባለማድረግ ምክንያት በዘርፉ ላይ ችግር ማጋጠሙን የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢብራሂም መሐመድ (ዶ.ር) አስረድተዋል።
በክልሉ 678 ሚሊዮን ብር ለሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተዘዋዋሪ ብድር መመቻቸቱንም ጠቁመዋል። የገበያ ማዕከላትን በማስፋፋት፣ በተዋንያን መካከል ትስስር በመፍጠር፣ የተሳለጠ እና ፍትሐዊ ግብይትን ማሳደግ በሚል መሪ መልዕክት ነው ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው። በውይይት መድረኩ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን እና የደብረ ብርሃን ከተማ ንግድ መምሪያ ኀላፊዎች፣ የዘርፍ ማኅበራት እና የንግድ ምክር ቤት ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፦ በላይ ተስፋዬ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!