የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪው ችግሮች እንዲፈቱ እገዛ ማድረጉ ተጠቆመ፡፡

35

ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን መምራት የሚያስችል ለሦስት ዓመታት የሚቆይ እቅድ ወደ ተግባር አስገብቷል። ይህን ተከትሎ የ2016 የአስር ወራት አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል፡፡

አፈጻጸሙ ከኩታ ገጠም አደረጃጀት አንጻር የመጡ ውጤቶችን ያመላከተ ነው። ከአቅም ግንባታ አንጻር በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች መሠራታቸውም ተነስቷል። በባለድርሻ ተቋማት ላይ የባለቤትነት ስሜትን መፍጠር መቻሉን፣ ንቅናቄው ብሔራዊ አጀንዳ እንዲኾን መደረጉን እና በየደረጃው የበላይ መሪዎች ልዩ ትኩረት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ተብሏል። ይህንን ያሉት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ፕሮጀከት ጽሕፈት ቤት አሥተባባሪ አያና ዘውዴ (ዶ.ር.) ናቸው።

ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ከሚቀርብ የፋይናንስ እና ግብአት አቅርቦት አንጻርም በየዓመቱ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የሚቀርበው የብድር መጠን የሥራ ማካሄጃ የፕሮክቶች ፋይናንስ ድጋፍ ለውጦች የተስተዋሉበት መኾኑም ተመላክቷል። ለአብነትም በ2014 በጀት 12 በመቶ የነበረው የብድር አቅርቦት መጠን በ2016 ወደ 16 በመቶ ከፍ ማለቱንም አሥተባባሪው ጠቁመዋል፡፡

የግሉ ዘርፍ እና ኢንቨስትመንት መሳብን በተመለከተም በርካታ ለውጦች መኖራቸውን የገለጹት አሥተባባሪው ለላፉት 10 ወራት 710 አዳዳስ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉን ገልጸዋል። የአነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱትሪዎች ሽግግር የተፋጠነ እንደነበር ጠቁመዋል።

ከመሠረተ ልማት አንጻርም የመሬት፣ የኃይል እና የትራንስፖርት አቅርቦት ቀልጣፋ የማድረግ ሥራው ውጤት የተመዘገበበት እንደነበር ጠቅሰዋል። ለአብነትም በክልል ከተሞች 12 ሺህ ሄክታር መሬት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የተላለፉበት እና ለ170 አምራች ኢንዱስትሪዎች የኃይል አቅርቦት ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠት የተቻለበት መኾኑን አንስተዋል፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በዋናነት ከተነሳበት የአምራች ኢንዱስትሪውን ማነቆዎችን ከመፍታት ዓላማ አንጻር ሲታይ በርካታ ለውጦች የመጡበት ነው መባሉን ኢዜአ አስነብቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በክልሉ ከ4 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ከ170 ሺህ በላይ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዙር ፈተና እየተፈተኑ ነው”ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)
Next article“ኢትዮጵያ በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል በተካሄዱት ሥብሠባዎች ስኬታማ ውይይቶችን አድርጋለች” አምባሳደር ነብዩ ተድላ