
ደባርቅ: መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሰሜን ጎንደር ደባርቅ ከተማ እየተካሄደ ነዉ። ሕዝባዊ ሰልፉ ፈተናን በመሻገር ሰላምን ለማጽናት እና ልማትን ለማስቀጠል የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ያለመ ነው።
በድጋፍ ሰልፉ መሪ መልዕክቶች ተስተላልፈዋል። ከመልእክቶች መካከልም:-
👉ዉስጣዊ ሰላማችን በማጽናት ዉጫዊ ተጽዕኖዎችን በድል እንወጣለን!
👉 ሰላማችን በእያንዳንዳችን ቤት ናት!
👉 የክልላችን ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እንፈልጋለን!
👉 የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድልና ስኬት የአባቶቻችን ገድል የደገምንበት ታሪካዊ አሻራ ነዉ!
👉 ኢትዮጵያ የዓድዋን ድል ዳግም እያደሰች ነዉ! የሚሉት ይገኙበታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!