በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውኃ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

17

ገንዳውኃ: መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውኃ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። በድጋፍ ሰልፉ ከተስተጋቡ ሕዝባዊ መልዕክቶች ውስጥ:-
👉 እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራችን ሠላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና የበኩላችንን እንወጣለን፤
👉 በጥቂት ጽንፈኛ ኃይሎች አስተሳሰብ እና እኩይ ድርጊት የሚበተን ሀገር እና ሕዝብ የለንም፤
👉 የላቀ ሕዝባዊ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብልፅግና፤
👉 ሀገራችንን ወደ ከፍታ ለማሻገር ከለውጡ አመራር ጋር በፅናት እንቆማለን፤
👉 ሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያን የታደገ እና ህልውናችንን ማስቀጠል ያስቻለ ነው፤
👉 ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የአንድነታችን እና የጥንካሬችን መገለጫ ነው፤
👉 በጠላቶቻችን የቆዬ ሴራ እና በተላላኪዎች ድንፋታ የብልጽግና ጉዟችን አይደናቀፍም፣
👉 ኢትዮጵያ የዓድዋን ድል ዳግም እያደሰች ነው የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች እየተስተጋቡ ይገኛሉ፡፡
ምንጭ:- የምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሰቆጣ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Next articleበአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ውስጥ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።