ምሥጋና🙏

39

“ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!” የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ
የበጎነት ተምሳሌቱን የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠን ዛሬ እናመሠግነዋለን።
ሚያዝያ 1968 ዓ.ም አዲስ አበባ ተወለደ ።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት በ1985 ዓ.ም አጠናቀቀ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1990 ዓ.ም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀበ።
ማስተዋል፣ ስክነት እና ለሰው መኖርን ከወላጆቹ የወሰደው ባሕሪይ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቤ ሕግ በመሆን ለ3 ዓመታት ሀገሩን እና ወገኑን በሐቅ እና በእኩልነት አገልግሏል ።

ወደ አሜሪካ በማቅናት በሚኒሶታ ሴንት ሜሪ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪውን በማጠናቀቅ በተለያዩ የንግድ ሥራዎች ላይ መንቀሳቀስ ጀመረ ።
አሜሪካ በቆየባቸው 7 ዓመታት ከሥራው ጎን ለጎን አረጋዊያን እና አቅመ ደካሞችን ለመርዳት የሚያስችለውን ትምህርት እና ገንዘብ ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ።

የተማረውን ዕውቀት እና ያጠራቀመውን ገንዘብ ይዞ አስታዋሽ ላጡ ሊደርስ የቅንጦት እና የምቾት ሕይወቱን ትቶ ወደ ሀገር ቤት ተመለሰ ።
በታኅሥሥ 2002 ዓ.ም ከአሜሪካ ተመልሶ በቤተሰቦቹ መኖሪያ ቤት የጀመረው በጎ ሥራ ከሁለት ዓመታት ልፋት በኋላ በ2004 እውን ሆነ ።
40 የሚሆኑ ተረጂዎችን በመያዝ “መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን ማዕከል” በሚል በ2004 ዓ.ም መሰረተ።
ይህ የበጎ አድራጎት ድርጅት ባለፉት 10 ዓመታት አርዓያ የሚሆን ተግባርን ፈጽሟል ።

“ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው” የሚል መርሕ አንግቦ የተነሳው የመቄዶንያ መሥራች ቢኒያም፣ ለሺዎች መጠለያ ዋርካ የሚሆን ተግባሩ ለብዙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አርዓያ መሆን የቻለ ነው ።
ለዚህ የሀገር ፍቅሩ እና አበርክቶው የበጎ ሰው ሽልማት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት አግኝቷል።

Previous article“ቅርብ ወራጅ 10 ብር …”
Next article“የመንግሥት ዓላማ ሕዝብን መጥቀም እና ዘላቂ ሰላምን ማምጣት ነው” ኢብራሂም ሙሐመድ (ዶ.ር)