
አዲስ አበባ: ጥር 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ከአፍሪካ መዲና እስከ ዓለም መድረክ ድረስ” የተሰኘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማሲ ፎረም በአዲስ አበባ ተከፍቷል።
ለ3 ሳምንታት የሚቆየው ይህ ፎረም የኢትዮጵያን የ3 ሺህ ዘመን የዲፕሎማሲ ጉዞ ታሪክ ለዕይታ አቅርቧል።
ፎረሙን የኢፌዴሪ ርእሰ ብሔር ሳሕለወርቅ ዘውዴ ከፍተውታል። በፎረሙ መክፈቻ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ.ር)፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ኢትዮጵያን ወክለው በተለያየ ሀገር የሚገኙ አምባሳደሮች፣ የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ርእሳነ መሥተዳድሮች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!