የኮሮና ቫይረስ ግብጽ መግባቱ ተረጋገጠ፡፡

162

ባሕር ዳር: የካቲት 07/2012 ዓ.ም (አብመድ) በቅርቡ በቻይና የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ግብጽ መግባቱ ተረጋግጧል፡፡

የግብጽ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው አንድ የውጭ ዜጋ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል፤ በሆስፒታል በልዩ ሁኔታ ለብቻው እየታከመም ይገኛል፡፡

የግብጽ ጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ግለሰቡ በበሽታው መያዙ ተረጋግጧል፤ መጀመሪያ ላይ ግን ምልክቶቹ አልታዩበትም ነበር፡፡ በበሽታው እንደተያዘ የታወቀውም የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተባቸው ሀገራት ለሚመጡ መንገደኞች በሚደረገው ተከታታይ ምርመራ ነው፡፡

ግለሰቡ የውጭ ዜጋ ከመባሉ በቀር የየት ሀገር ዜጋ እንደሆነና ከየት ተነስቶ በየት በኩል ግብጽ እንደገባ በዘገባው አልተመላከተም፡፡ ግብጽ ከአፍሪካ አህጉር ኮሮና ቫይረስ እንደተከሰተ የተረጋገጠባት የመጀመሪያዋ ሀገር ናት፡፡

ኮሮና ቫይረስ እስካሁን ከ1ሺኅ 500 በላይ ቻይናውያንን ህይወት ቀጥፏል፡፡ ከቻይና ውጭ ካሉ ሀገራት በቫጥረሱ የተያዙትን ጨምሮ ጨምሮ በበሽታው የተያዙት ደግሞ 65 ሺኅ መድረሱ ተዘግቧል፡፡ ቫይረሱ ከቻይና ውጭ በ25 ሀገራት መስፋፋቱንም የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

ትኩስና ተከታታይ መረጃዎችን ለማግኘት በእነዚም አማራጮች ይከታተሉን፡፡
ቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዮቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC

በአብርሃም በዕውቀት

ምንጭ፡- አልጀዚራ

Previous articleከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የወረታ ደረቅ ወደብ እና ‹ተርሚናል› ግንባታ ተመረቀ።
Next articleያልዘመነው የቱሪዝም ዘርፍ ዜጎች ይበልጥ እንዳይጠቀሙ አድርጓል፡፡