ኢትዮ-ቴሌኮም ቀላል እና ምቹ የትራንስፖርት እና ነዳጅ አቅርቦትን የሚያዘምን ሶሊሽን ይዞ መምጣቱን አስታውቋል።

44

አዲስ አበባ: ኅዳር 7/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮ-ቴሌኮም ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን፣ ከመንገድ ደኅንነት እና መድኅን ፈንድ አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ጋር በመተባበር የትራንስፖርት እና ነዳጅ አቅርቦቱን የማዘመን ዲጅታል ሶሊሽን ይፋ አድርጓል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ድኤታ በሪሁ ሁሴን፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ጀኔራል ዳይሬክተር ሰረላ አብደላህ፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ሥራ አሥኪያጅ እስመለዓለም ምህረቱ እና የመንገድ ደህንነት ፈንድ አገልግሎት ሥራ አሥፈጻሚ ጀማል አባሶ ተገኝተዋል።

ኩባንያው ከባለድርሻ አካላት ጋር የነዳጅ እና አቅርቦት ሠንሰለት፣ የነዳጅ፣ የኩፖን እና የሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ዲጅታል ለማድረግ የሚያስችሉ አሠራሮችን ይፋ ማድረጉን ገልጸዋል።

ኩባንያው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር፣ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ጋር በመተባበር የነዳጅ አቅርቦት የአሠራር ሥርዓቱን እና የነዳጅ ኩፖንን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችል ሥራ እየሠራ ነው፡፡

እንዲኹም ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ከመንገድ ደኅንነት እና ኢንሹራንስ ፈንድ አገልግሎት ጋር የሦስተኛ ወገን የመድህን አገልግሎትን ዲጂታላዝ ለማድረግ ሶልሾኖችን በይፋ አሥጀምረዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ኩባንያው የነዳጅ ሽያጭ የኩፖን አገልግሎት አሠራርን ወደ ወረቀት አልባ የዲጅታል ኩፖን በመቀየር አዲስ አሠራርን ዘርግቷል ብለዋል።

ይኽን ዘመናዊ የዲጅታል አሠራር የነዳጅ ኩባንያዎች የአገልግሎት አሠጣጥ ለማዘመን፣ የነዳጅ ማደያዎች የአገልግሎት አማራጭ ለማሣደግ፣ የተጠቃሚዎችን መጠን ለመጨመር ያግዛል ብለዋል።

ኩባንያው የሦስተኛ ወገን የመድህን አገልግሎት በዲጅታል ሥርዓት አማካኝነት ለመሥጠት የሚያስችል ሶሉሽን ከትራንስፖርት እና ሎጄስቲክስ ሚኒስቴር እና ከመንገድ ደኅንነት እና መድህን ፈንድ ጋርም በመተባበር ይፋ ማድረጉ ለኢንሹራንስ አሠጣጥ ጋር የሚነሱ ውስንነቶችን በማስቀረት የተማከለ መረጃ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ይህን የነዳጅ ዲጅታላይዜሽን ዘመናዊ አሠራርን ለመተግበር እና የትራንስፖርት እና የነዳጅ አቅርቦት ለማዘመን እንደሚሠሩም ገልፆም።

ዘጋቢ፦ እዮብ ርስቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የደቡብ ሱዳን ሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲኾን ኢትዮጵያ ገንቢ ሚና ትጫወታለች” አቶ ደመቀ መኮንን
Next articleሌላ ጫና አንችልም፤ ሰላም ነው የምንፈልገው” የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች