
ባሕር ዳር: ኅዳር 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በዛሬው እለት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንሰቲትዩት በመገኘት ለሁለት ወራት ስለሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ ምንነት እና ጠቀሜታ ስልጠና ተከታትለው የተመረቁ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችን ተመልክተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው “ልጆቻችን የኢትዮጵያን ችግሮች በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ ለመፍታት ቁልፍ የሆነውን እውቀት መገብየታቸው ተስፋ ሰጭ ነው” ብለዋል፡፡ ልጆች የኢትዮጵያን ችግሮች በሰው ሰራሽ አስተዉሎት በመታገዝ ለመፍታት ቁልፍ የሆነዉን እዉቀት መገብየታቸዉ ተስፋ ሰጭ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በልጆቹ አቅም በመገረም የሀገራችንን እድገት ለማረጋገጥ እንደሚችሉ ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!