“እንደ ክልል ያጋጠመውን የሰላም እጦት በዘላቂነት ለመፍታት የክልሉ መንግሥት በትኩረት እየሠራ ነው” ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ

78

ባሕር ዳር: ጥቅምት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ በሀገራዊና ክልላዊ ኹኔታዎች ዙሪያ ከተለያዩ አካላት ጋር በደሴ ከተማ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱም የወሎና አካባቢው ማኅበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመኾን የአካባቢውን ሰላም የሚጠብቅበት መንገድ ለሌሎች አካባቢዎችም ተሞክሮ እንደሚኾን ነው የገለጹት፡፡

የደሴና አካባቢው ማኅበረሰብ እንደሌሎች አካባቢዎች ሁሉ የልማትና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች እንዳሉት ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ተናግረዋል፡፡

ርእሰ መሥተዳድሩ ኅብረተሰቡ ጥያቄዎቹን በየደረጃው በሰላማዊ መንገድ በማቅረብ እና የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ እያደረገ ስላለው አስተዋጽኦ በክልሉ መንግሥት ስም አመሥግነዋል፡፡

እንደ ክልል ያጋጠመውን የሰላም እጦት በዘላቂነት ለመፍታት የክልሉ መንግሥት በትኩረት እየሠራ መኾኑን አንስተዋል፡፡

ርእሰ መሥተዳድሩ መንግሥት ከሕዝቡ ጋር በመተባበር እየወሰደው ባለው እርምጃና በተደረገው ውይይት ክልሉን ወደ ሰላም ለማምጣት እየተሠራ ስለመኾኑም አስገንዝበዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎችም ርእሰ መሥተዳድሩ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በደሴ ከተማ ተገኝተው ከኅብረተሰቡ ጋር መወያየታቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡

ከግጭት አዙሪት በመውጣት ሁሉም ለሰላም ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባልም ብለዋል፡፡

አንድነትን በማስቀጠል ኅብረ ብሔራዊነትን ማስጠበቅ አለብን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ማህሌት ተፈራ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከደሴ ከተማ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ።
Next article“የምክክር ሀገር ጠንካራ ነው”