
ባሕር ዳር: መስከረም 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 498ኛው የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል በባሕርዳር ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ በበዓሉ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ እና መልካም ምኞት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ምክትል ከንቲባው በዓሉ ባለፉት ጊዜያት ያጋጠሙ አሉታዊ ገጽታዎችን አስወግደን፣ በአዲስ መንፈስ እና በጋራ ደምቀን የምናከብረው ነው ብለዋል። መውሊድን ስናከብር ደጋፊ ለሌላቸው ወገኖች ማዕድ በማጋራት እና ፍቅርን በመስጠት መኾን እንደሚገባም ተናግረዋል።
በሰላም እጦት ምክንያት የሚቸገሩ ወገኖች ስለመኖራቸው የጠቀሱት ምክትል ከንቲባው ሰላም እንዲሰፍን በአዲስ ተስፋ እና አብሮነት መሥራት አለብን ብለዋል። በባሕርዳር ከተማ አሁን ያለውን አንጻራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላም ለማሸጋገር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!