በደብረ ብርሃን ከተማ የ2016 ዓ.ም ትምህርት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተጀመረ።

73

ባሕርዳር፡ መስከረም 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ መቅደስ ብዙነህ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ መጀመሩን አስረድተዋል።

ወይዘሮ መቅደስ በከተማው በአጠቃላይ 81 የትምህርት ተቋማት አሰካሁን ከ40 ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ መረጃ በደብረብርሃን ከተማ በኃይለማሪያም ማሞ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2016 በጀት አመት ትምህርት ተጀምሯል።

የትምህርት ቤቱ ርዕሳነ መምህራን ፣ መምህራን ፣ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል።

የኃይለማሪያም ማሞ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ንጉሥ ደስታ እንዳነሡትም በ2016 በጀት አመት በትምህርት ቤታችን 1ሺህ 317 ነባር እና አዲስ ተማሪዎችን እናስተምራልን ብለዋል።

የከተማ አሥተዳደሩ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ መረጃ እንደሚያሳየው 86 መምህራን በትምህርት ቤቱ እንደሚገኙና ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍለ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የሚያስተምሩ መሆኑንም አቶ ንጉሥ ጠቁመዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአዲሱ የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤት ለማምጣት ተዘጋጅተናል”ተማሪዎች
Next article“ከግጭት አዙሪት ወጥቶ ወደ ሰላም ከፍታ ለመሻገር የሁላችን ርብርብ እና መደማመጥ ያስፈልጋል” ኮሎኔል ኤፍሬም ተስፋየ