እየታየ ያለው አንፃራዊ ሰላም እንዲጠናከር ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት አሳሰበ።

50

ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ግምገማ አካሂዷል።

በግምገማው ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የሰሜን ሸዋ ዞን አመራሮችና የኮማንድ ፖስቱ አባላት ተገኝተዋል።

ኮማንድ ፖስቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸሙ ላይ ውይይት ያደረገ ሲኾን የታዩ ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶችም ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ቀጣይ በሚሰጡ የአመራር ስምሪቶችና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

እየታየ ያለው አንፃራዊ ሰላም እንዲጠናከር ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ርብርብ ይደረጋል ተብሏል።

የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዲየር ጄነራል አበባው ሰይድ እና በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ ዶክተር አህመዲን መሀመድ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።

ዘጋቢ፡- ኤልያስ ፈጠነ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከመምህራን ማኅበር አመራሮች ጋር ተወያዩ።
Next articleሲኒካ አንቲላ (ዶ.ር) በኢትዮጵያ የፊንላንድ ሪፐብሊክ አምባሳደር ኾነው ተሾሙ::