
ባሕር ዳር: ነሐሴ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ አቧሬ አካባቢ በክረምቱ ወቅት የታደሱ ቤቶችን ለዐቅመ ደካሞች እና ለአረጋውያን ዛሬ ጠዋት አስረክበዋል።
በዚህ ዓመት ግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ የ2015 ዓመታዊ የቤት እድሳት መርሐ ግብርን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማስጀመራቸው ይታወሳል።
በአጭር ጊዜ ውስጥ በፍጥነት እና በጥራት የተገነባው ሕንጻ ሱቆችንም ማካተቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!