30 ሚሊዮን በሚጠጋ ወጪ የተገነባው የናኒና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።

63

ባሕር ዳር: ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ 30 ሚሊዮን በሚጠጋ የክልሉ በጀት የተገነባው የናኒና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው ተጠናቅቆ ዛሬ ለምረቃ በቅቷል።

በወረዳው አንድ ብቻ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያለ በመኾኑ አሁን የተገነባው ይህ አዲስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በማድረግ ከትምህርት ገበታቸው ይፈናቀሉ የነበሩ ተማሪዎችን ይታደጋል ተብሏል።

ትምህርት ቤቱ 2 ብሎክ የመማሪያ ህንጻ፣ ዘመናዊ ቤተ መጽሐፍ፣ አንድ የአሥተዳደር ህንጻ ፣ የአይሲቲ ማዕከል እና የቤተ ሙከራ ማዕከል ያካተተ ነው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ መኳንት አደመ፣ በክልሉ ምክር ቤት የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በላይ ዘለቀ ፣ የሰሜንና ምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ፣ የወረዳ መሪዎችና የአካባቢው ማኀበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።

ዘጋቢ:- ዘመኑ ይርጋ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን የመጡ ምሁራን የዩኒቨርሲቲው መጠሪያ ስም የኾነውን የመቅደላ ተራራን ጎበኙ።
Next article“መጻዒ እጣ ፋንታችን የሚወሰነው በሌሎች ይኹንታ ሳይኾን በራሳችን አቅም ነው” አቶ አታላይ ታፈረ