“በበጀት ዓመቱ የሳይበር ጥቃቶችን በመከላከል 23 ነጥብ 2 ቢልዮን ብር ማዳን ተችሏል” የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሥተዳደር

35

ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በበጀት ዓመቱ የሳይበር ጥቃቶችን በመከላከል 23 ነጥብ 2 ቢልዮን ብር ማዳን መቻሉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሥተዳደር አስታወቀ፡፡

የአሥተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ላይ ስድስት ሺህ 959 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝረው 96 ነጥብ ሁለት በመቶውን መመከት ተችሏል፤ ቀሪውም በሂደት ላይ ይገኛል፡፡
ጥቃቶቹ ባይመከቱ ኖሮ በሀገር ላይ የሚያደርሱት ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲያዊና ሥነል ቦናዊ ኪሳራ ከፍተኛ እንደሚኾን ገልጸዋል ዋና ዳይሬክተሩ።

እንደ ኢፕድ ዘገባ ጥቃቶችን በመከላከሉ ከሀገሪቱ ካዝና ሊወጣ የሚችል 23 ነጥብ ሁለት ቢልዮን ብር ማዳን ስለመቻሉም ነው ያመላከቱት።

የጥቃት ኢላማዎች የፋይናንስ ተቋማት፣ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት፣ ሚዲያዎች፣ ቁልፍ የመንግሥት ተቋማት፣ ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የክልል ቢሮዎች፤ የህክምና እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጥቃት ኢላማዎች እንደነበሩ ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ዳሬ ሰላም ገባ
Next article“አማራ ነን የምንለው ከአማራነት ወጭ ሌላ ማንነት ስለሌለን ነው” ክብረአብ ስማቸው