
ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መነሻውን ከጅቡቲ ወደብ አድርጎ መዳረሻውን ወረታ ከተማ ለማድረግ የተንቀሳቀሰው 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የጫነ ተሳቢ ተሽከርካሪ ከታሰበው ቦታ ሳይደርስ አሽከርካሪው ከግለሰቦች ጋር በመመሳጠር ሕገ ወጥ ተግባር ሲሰራ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ሕገ ወጥ ድርጊቱ የተፈጸመው በባሕር ዳር ከተማ ሰባታሚት ቀበሌ ሀምሌ 16 ቀን 2015 ዓ/ም ነው። ከሌሊቱ 6:00 የአፈር ማዳበሪያውን በሕገ ወጥ መንገድ ለግለሰቦች ሲያከፋፍል በኅብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን የሰባታሚት ቀበሌ ፖሊስ ኦፊሰር ኮንስታብል ዮሐንስ ጥላሁን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ ትርንጎ ይፍሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!