
ባሕር ዳር: ሐምሌ 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሥራ ዕድል ፈጠራ የኢትዮጵያ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሁሉም አፍሪካዊ ጉዳይ ነው ሲሉ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ፡፡
የአፍሪካ የሥራ ፎረም የአፍሪካ አሕጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ለኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማትና ማስፋፋት ያለው መልካም ዕድሎችና ፈተናዎች በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል÷አፍሪካ በውስጧ እምቅ ሃብት ያላት አህጉር በመሆኗ የመልማት እድሎችን አፍሪካውያን በጋራ መጠቀም ይኖርብናል ብለዋል፡፡
የስራ ባህል ለውጥ ላይ ትኩረትን ያደረጉ ሀገራት ዛሬ ላይ ስኬት ላይ ደርሰዋል ያሉት ሚኒስትሯ÷አፍሪካዊያንም ካለፉት ችግሮቻችን ተምረን ጥቅም ላይ ያልዋለውን ጉልበት ወደ ሃብት መቀየር ይገባነናል ብለዋል።
ፋና እንደዘገበው 3ኛ ቀኑን የያዘው የአፍሪካ የስራ ጉባዔ አንዱ መርሃ ግብር በሆነው በዚህ መድረክ የአፍሪካ ኤሌክትሮኒክስ ንግድ ቡድን ተሳታፊዎች እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!