የ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀት 801 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ኾኖ በምክር ቤቱ ጸደቀ፡፡

75

ባሕር ዳር: ሰኔ 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ጉባዔ የ2016 የፌዴራል መንግሥት በጀት ዓዋጅ ቁጥር 1297/2015 ኾኖ ጸድቋል፡፡ የ2016 በጀት ዓመት በጀት 801 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ኾኖ ጸድቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2016 በጀት ትኩረት ላይ ያደረገው ጉባዔው የ2016 በጀት ዓመትን ዓመታዊ በጀት አጽድቋል፡፡

ካለፈው በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀት ጋር ሲነጻጸር 1 ነጥብ 9 በመቶ ብልጫ ያለውን የ2016 በጀት የምክር ቤት አባላቱ ተወያይተው በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የዋህ ዜጎች፣ ሌባ ደላሎች እና ነጋዴ ሹመኞች የፈጠሩትን ሕገ-ወጥ ድርጊት ለማረም ተስማምተናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
Next article“የራሳችን አቅም ዋና አንቀሳቃሻችን፣ ዓለም ባንክ ደግሞ ደጋፊያችን ነው” የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ ቢያዝን እንኳሆነ