አግራ ኢትዮጵያ በግብርናዉ ዘርፍ እገዛ እንደሚያደርግ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአግራ የቦርድ ስብሳቢ ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ።

40

አዲስ አበባ:: ሰኔ 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አግራ ኢትዮጵያ በግብርናዉ ዘርፍ ሀገሪቱ የጀመረችዉን የለዉጥ ጉዞ በመደገፍ ግብርናን ለማዘመን እንደሚሠራ ነው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የአግራ የቦርድ ስብሳቢ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተናገሩት።

“የአፍሪካ አረንጓዴ የአብዮት ጥምረት” (አግራ) በኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በግብርና እና በምግብ ዋስትና ላይ ለመሥራት ያቀደዉን የ5 ዓመት ስትራቴጅ አስተዋዉቋል።

በ2006 ዓ.ም የተመሰረተዉ አግራ በአፍሪካ በ15 ሀገራት ከ26 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች የአየር ንብረት ለዉጥን ተቋቁመዉ ማምረት እንዲችሉ ለማድረግና በግብርናዉ ዘርፍ ለዉጥ እንዲመጣ መሥራቱን አስታዉቋል።

ለአፍሪካዉያን ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ መስጠት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መኾኑንም አስገንዝበዋል። አግራ በኢትዮጵያ ያስተዋወቀዉ የ5 ዓመት እቅድ ኢትዮጵያዉያን እራሳቸዉን በምግብ እንዲችሉ እና ግብርናን ለማዘመን የሚያስችል ነዉም ተብሏል። የአግራ የቦርድ ሰብሳቢ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አግራ በኢትዮጵያ የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማዘመን እና የመሬት መሸርሸርን ለመከላከል የሠራቸዉ ሥራዎች የሚደነቁ ናቸው ብለዋል፡፡ ለዚህም ለኢትዮጵያ መንግሥት እዉቅና መስጠት ያስፈልጋል፤ አግራም ይህንን ዘርፍ ለመደገፍ ይሠራልም ነዉ ያሉት። አግራ በቀጣይ 5 ዓመት በኢትዮጵያ የሀገሪቱን የግብርና አጀንዳ በመደገፍ እና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የግብርናው ድርሻ እንዲጨምር ማድረግ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራም ተናግረዋል። የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ስትራቴጅዉ የራሱን ድርሻም ይወጣል ነው ያሉት።

ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በዘንድሮው ዓመት 12 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ተገዝቷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“የዋህ ዜጎች፣ ሌባ ደላሎች እና ነጋዴ ሹመኞች የፈጠሩትን ሕገ-ወጥ ድርጊት ለማረም ተስማምተናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ